ማየት ለተሣናቸው የዴሥክ ቶፕ አክሰስ (NVDA) ነጻ እና ግልጽ ምንጭ የሆነ ለማይክሮሦፍት ኦፕሬቲንግ ሢስተም የእስክሪን ማንበቢያ ነው። በድምጽ እና በብሬል በመታገዝ ማየት የተሣናቸው ሠዎች ኮንፒተርን በመጠቀም ዊንዶው ሌሎች የሚያዩ ወገኖች እንደሚጠቀሙት ያለ ምንም ክፍያ መገልገል ይችላሉ። NVDA የተቀመረው በ ማየት በተሣነው አክሰስ, በማህበረሠቡ ዐሥተዋጽኦ ነው።
NVDA ማየት ለተሣናቸው የዊንዶው ኦፕሬቲንግ ሢሥተምን እና ሌሎች ሶስተኛ ወገን ፕሮግራሞችን መጠቀም ያሥችላል።
የዋነኛ ትኩረቶች ማእቀፍ:
ሠዎች በየትኛውም የዐለም ክፍል ቢኖሩ ማናቸውንም ቋንቋ ቢናገሩ ኮንፒተርን በተሥማሚ ሁኔታ መጠቀማቸው ትኩረት ሊሠጠው ያሥፈልጋል። NVDA ከእንግሊዘኛ በተጨማሪ b40 ቋንቋዎች ተተርጉሟልa እነዚህም: አፍሪካን, አልባኒያን, አማርኛ, አረብኛ, ብራዚል ፖርቺጊዝኛ, ቡልጋርያኛ, ኮሬሻንኛ, ቼክኛ, ዴንማርክኛ, ዳችኛ, ፊንላንድኛ, ፈረንሣይኛ, ጌሊሽኛ, ግሪክኛ, ጆርጃኛ, ጀርመንኛ, ሂብሩኛ, ህንድኛ, ሀንጋርኛ, አይሥላንዲክኛ, ጣሊያንኛ, ጃፓንኛ, ኮሪያኛ, ኔፖሊኛ, ኖርዌጃንኛ, ፖላንድኛ, ፖርቱጋልኛ, ሮማንኛ, ሩሢያኛ, ሰርቢያኛ, ሥሎቫክኛ, እስፓንሽኛ, ሥዊዲንኛ, ታሚልኛ, ታይኛ, የጥንቱ እና ዘመናዊው ቻይንኛ, ቱርክኛ, ኡክራንኛ እና ቬትናምኛ።
በተጨማሪም ለኢንተርፌስ እና ለልዩልዩ ቊንቊዎች ድጋፍ ከማድረጉም በላይ, NVDA ማናቸውንም የጽሁፍ ይዘት ለማንበብ ያሥችላል የእስፒች ሢንተሣይዘሩ በእዚያ ቊንቊ እስከታቀፈ ድረሥ።
NVDA እንዲህ ተጣምሯል eSpeak, ነጻ, ክፍት-ግልጽ, መድብለ--ልሣን የሆነ እስፒች ሢንተሣይዘር ነው። NVDA ሥለሚያቅፋቸው ሌሎች እሥፒች ሢንተሣይዘሮች መረጃ እንዲህ ማግኘት ይቻላል [#ታቃፊ እሥፒች ሢንተሣይዘሮች] ክፍል.
የብሬል ገበታ ወይንም ብሬል ዲስፕሌ ተጠቃሚዮች NVDA መረጃዎችን በብሬል ያቀርባል። እባክዎን በማእቀፉ ውሥጥ የሚገኙትን የብሬል ገበታ ይመልከቱ [ማእቀፉ ውሥጥ ያሉት ብሬል ገበታዎች #ማእቀፈ ብሬል ገበታ] ክፍል ለመረጃ ስለ ታቀፉት የብሬል ገበታዎች። NVDA የብዙ ቋንቋዎች ብሬል ኮድ ያቅፋል, እነዚህም ማሣጠሪያ, ያለማሣጠሪያ እና ኮንፒተር ብሬል ኮዶች ለብዙ ቋንቋዎች።
የNVDA ሕጋዊ መብት 2006-2023 የNVDA ዐሥተዋጽኦ አድራጊዎች።
NVDA በአዲሱ አጠቃላይ የሕዝባዊ ፈቃድ ይሸፈናል (Version 2). ይህንን ሦፍትዌር በማንኛውም መንገድ በነጻነት ለማሠራጨት እና ለመለወጥ ይችላሉ የሕጋዊነቱን ፈቃድ እና ምንጩን አብረው ለሚፈልገው ተጠቃሚ እሥከ ሠጡ ድረሥ። ይህም ለዋናውም ሆነ ለተለወጠው የሦፍትዌር ኮፒ, በተጨማሪ የታከለበትን ስራ ይመለከታል። ለተጨማሪ ዝርዝር, እዚህ ይመልከቱ ስለሙሉ ፈቃዱ።
ሥያሜ | ቁልፍ | መግለጫ |
---|---|---|
አቁም ንግግር | ኮንትሮል | ወዲያው ንግግር ያሥቆማል |
መግቻ ንግግር | ሽፍት | ወዲያው ይገታል ንግግር። ደግመው ሢጫኑትከተገታበት ቦታ ጀምሮ መነጋገር ይጀምራል (መግቻው አሁን የተተከለው ሢnneተሣይዘር የሚደግፈው ከሆነ) |
NVDA ሜኑ | NVDA ድምር N | ይከፍታል የNVDA ሜኑ ይኸውም አማራጭን አክሰስ ለማድረግ, ቱልስ እና እገዛ ወዘተ |
የንግግር መለዋወጫ ሁኔታ | NVDA ድምር S | የንግግሩን ሁኔታ በእነዚህ መካከል ይለዋውጣል, ንግግር, ጢጥ እና ማጥፋት። |
የእገዛ ኪቦርድ መለዋወጫ ሁኔታ | NVDA ድምር 1 | በእዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ማንኛውንም ቁልፍ ቢመቱ ስለ ቁልፉ, መግለጫ እና ማንኛውንም ከNVDA ጋር የተያያዙትን ማዘዣዎች ይነግሮታል። |
ማቋረጥ NVDAን | NVDA ድምር Q | NVDAን ይዘጋል |
በቀጣዩ ቁልፍ ውሥጥ ሥለማለፍ | NVDA ድምር F2 | ምንም እንኳን ቁልፉ እንደ NVDA እንዲሰራ ቢታዘዝ, በእዚህ ሁኔታ ቁልፉ እንደማንኛውም ቁልፍ ይሰራል |
አፕሊኬሽኑን አሣርፍ በሚለው ሁኔታ በመለዋወጥ ማብራት እና ማጥፋት | NVDA ድምር ሽፍት ድምር S | ይህ ትእዛዝ NVDAን በማሣረፍ, የንግግርም ሆነ የብሬል ስራ ያቋርጣል። ይኸውም ሌላ የእሥፒች ሢንተሣይዘር ካለ ለመጠቀም ያሥችላል። ነገርግን ይህ ትእዛዝ እንደገና ከተሠጠ, ወደ ቀድሞው ስራው ይመለሣል |
ሥያሜ | ቁልፍ | መግለጫ |
---|---|---|
ቀን እና ሠዐት ማሣወቂያ | NVDA ድምር ኤፍ 12 | አንዴ ሢመቱት ሠዐት ይነግራል, ሁለተኛ በፍጥነት ሢመቱት ቀን ይነግራል |
የባትሪውን የጉልበት አቅም ማሣወቂያ | NVDA ድምር ሽፍት ድምር B | የባትሪውን ጉልበት ምንም እንኳን ኤሌትሪክ ተሠክቶም ቢሆን ምን ያህል እንደሞላ በፐርሠንት ያሣውቃል |
በክሊፕቦርድ ላይ ያለውን ቴክስት ማሣወቂያ | NVDA ድምር C | በክሊፕቦርዱ ላይ ማንኛውም ትቴክስት ከተቀመጠ ያሣውቃል። |
ኤንቪዲa ሢስተሙን በብዙ መንገድ ለማሰስ እና ለመቃኘት በመደበኛም ሆነ በግምገማ አካሄድ ያሥችሎታል።
እያንዳንዱ አፕሊኬሽን እና ሲስተም መዘውሩ ብዙ የእየራሡን ዖብጀክት ይይዛል።
ዖብጀክት ማለት እንደ ጽሁፍ, ባተን, አመልካች ሣጥን, ስላይደር, ዝርዝር ወይንም በጽሁፍ የሚሞላ መሥመር ናቸው።
++ የሲስተም ቅኝት በትኩረት ++[ሲስተም በትኩረት] የሲስተም ትኩረት ማለት, በቀላሉ ትኩረትን ያው ትኩረት ማለት ነው, [ዖብጀክቶች #ዖbj,ክት] ታይፕ ሢደረግ በኪቦርዱ ላይ መቀበል ሢችል ማለት ነው። ለምሣሌ, ታይፕ በሚያደርጉበት የመጻፊያው ስፍራ ላይ, ጽሁፉ በመክተቢያው ሜዳ ላይ ትኩረት ኣለው ማለት ነው። በጣም የተለመደው የዊንዶው ሲስተም ቅኝት በኤንፂዲኤ, የሲስተሙን ትኩረት በመደበኛው የዊንዶው ቁልፍ ማዘዣ እንደ ታብ እና ሽፍት ታብ በመጨቆን ወደፊት እና ወደሗላ መሄድ, ኦልትን በመጨቆን የሜኑ አሠላለፎችን መክፈት, በኣፕ እና በዳውን አሮው መቃኘት, እንዲሁም ኦልት እና ታብን ባንድነት በመጨቆን የተከፈቱ ፕሮግራሞችን መመልከት። ይህንን በሚያደርጉበት ግዜ, NVDA ትኩረት ያለበትን ዖብጀክት ይገልጽሎታል, እንደ ሥም, አይነት, ዋጋ, ሁኔታ, መግለጫ, የቁልፍ አቋራጭ መንገዶች እና አቀማመጣቸውን ይገልጻል። የሲስተሙን ትኩረት ለማወቅ የሚያሥችሉ ጥቂት ጠቃሚ የቁልፍ ማዘዣዎች አሉ:
ሥያሜ | ቁልፍ | መግለጫ |
---|---|---|
አሁን በትኩረት ላይ ያለውን መግለጽ | NVDA ድምር ታብ | ወቅታዊውን ዖብጀክት ያሣውቃል ወይንም የሲስተሙን ትኩረት ይቆጣጠራል። ሁለት ግዜ መታመታ ሢደረግ መረጃውን ፊደል በፊደል ያነባል |
ያሉበትን ሁኔታ ገላጭ | NVDA ድምር T | ይህንን ቁልፍ ሢጨቁኑ, NVDA አሁን ዊንዶው ያለበትን ሁኔታ ይገልጻል። በፍጥነት ሁለት ግዜ መታመታ ሢያደርጉ መረጃውን ፊደል በፊደል ያነባል። ሶስተኛ ግዜ መታመታ ሢያደርጉ, መረጃውን ወደ ክሊፕቦርድ ይገለብጣል |
ተከፍቶ ስራ ላይ ያለውን ዊንዶው አንባቢ | NVDA ድምር B | ተከፍቶ በስራ ላይ ያለውን የሁሉንም የዊንዶው መቆጣጠሪያ ያነባል (ጠቃሚ ነው ለዳያሎጎች።) |
ያሉበትን ሁኔታ ማሣወቂያ | NVDA ድምር END | ያሉበትን ሁኔታ NVDA ካገኘ ያሣውቃል። ደግሞም ዖብጀክት መቃኛውን ወደ እዚሁ ሥፍራ ያንቀሳቅሠዋል |
++ መቃኘት በሲስተም ጠቋሚ ++[ሲስተም ጠቋሚ] ዖብጀክቱ ወይንም ዖብጀክቶቹ የሲስተሙን ትኩረት ሢያገኙ, በሲስተም ጠቋሚው መቃኘት ይቻላል, ወይንም የሲስተሙ መክተቢያ ጠቋሚ እየተባለም ይጠራል። ትኩረቱ ዖብጀክቱ ላይ ካረፈ እና የሲስተሙ ጠቋሚ በቀስቶቹ አማካኝነት, አፕ አሮው, ሆም, ዳውን አሮው, ኤንድ ወዘተ በመጠቀም በጽሁፉ ውሥጥ መንቀሣቀሥ ይቻላል። የቁጥጥር ቁልፍን በመጨመር, የጽሁፉን ሁኔታ መለዋወጥ ይቻላል። ይኸውም NVDA በፊደል, በቃላት, በመሥመር ጽሁፉ መንቀሣቀሡን ይገልጻል, እንዲሁም ጽሁፉ መመረጡን ወይንም አለመመረጡን ይገልጻል።
NVDA ከእዚህ ቀጥሎ የሲስተም ጠቋሚውን ማዘዣ ቁልፎች ያቀርባል:
ሥያሜ | ቁልፍ | መግለጫ |
---|---|---|
ሁሉንም ተናገር | NVDA ድምር ቀስት ወደ ታች | የሲስተሙ ጠቋሚ ከሚጀምርበት አንሥቶ ጽሁፉ እሥከሚያበቃበት ድረሥ ያነባል |
አንብብ ያረፈበትን መሥመር | NVDA ድምር ቀስት ወደ ላይ | የሲስተሙ ጠቋሚ ያረፈበትን መሥመር ያነባል። ሁለት ግዜ መታመታ ሲደረግ, መሥመሩን ፊደል በፊደል ያነባል። |
አንብብ አሁን የተመረጠውን ጽሁፍ | NVDA ድምር ሽፍት ድምር ቀስት ወደ ላይ | NVDA ማንኛውንም አይነት የተመረጠ ጽሁፍ ያነባል |
ወደ ሠንጠረዥ ውሥጥ ሢገቡ የሚጠቀሙባቸው የማዘዣ ቁልፎች ደግሞ እነሆ:
ሥያሜ | ቁልፍ | መግለጫ |
---|---|---|
ወደ ቀዳማይ ኮለም አንቀሣቅሥ | ቁጥጥር ድምር ዖልት ድምር ግራ ቀስተኛ | የሲስተሙን ጠቋሚ አሁን ካለበት ስፍራ ወደ ቀዳማይ ኮለን ያንቀሣቅሣል (ነገርግን ባለበት ተራ መሥመር ውሥጥ ነው) |
ወደ ታችኛው ኮለም አንቀሣቅሥ | ቁጥጥር ድምር ዖልት ድምር ቀኝ ቀስተኛ | የሲስተሙን ጠቋሚ አሁን ካለበት ስፍራ ወደ ታችኛው ኮለን ያንቀሣቅሣል (ነገርግን ባለበት ተራ መሥመር ውሥጥ ነው) |
ወደ ቀዳማይ ተራ መሥመር አንቀሣቅሥ | ቁጥጥር ድምር ዖልት ድምር ቀስት ወደ ላይ | የሲስተሙን ጠቋሚ አሁን ካለበት ስፍራ ወደ ቀዳማይ ተራ መሥመር ያንቀሣቅሣል (ነገርግን ባለበት ኮለን ውሥጥ ነው) |
ወደ ታችኛው ተራ መሥመር አንቀሣቅሥ | ቁጥጥር ድምር ዖልት ድምር ቀስት ወደ ታች | የሲስተሙን ጠቋሚ አሁን ካለበት ስፍራ ወደ ታችኛው ተራ መሥመር ያንቀሣቅሣል (ነገርግን ባለበት ኮለን ውሥጥ ነው) |
በአብዛኛው ግዜ በሲስተሙ የሚገለገሉበት ትእዛዝ በሚጠቀሙት የፕሮግራም ክፍሎች ነው, ይኸውም ያንቀሣቅሣል «የሲስተም ትኩረት» እና «የሲስተም ጠቋሚ» ነገርግን የሚገለገሉበትን ፕሮግራም የሲስተሙ ትኩረት እና ጠቋሚ ሣይንቀሣቀሡ ማወቅ ይፈልጉ ይሆናል። በተጨማሪም «በዖብጀክት» መስራት ይፈልጉ ይሆናል, ይህ በተለምዶ በኪቦርድ አመቺ አይደለም። በእዚህ ግዜ ታድያ የዖብጀክት መቃኛን መጠቀም ይችላሉ።
የዖብጀክት መቃኛው የእያንዳንዱን ዖብጀክት እና በውሥጡ ያሉትንም መረጃዎች በማንቀሣቀሥ መጠቀም ያሥችላል። ወደ ዖብጀክቱ ሢንቀሣቀሡ, NVDA የሲስተሙ ትኩረት ሢንቀሣቀሥ እንደሚነግረው ይህንንም ይገልጻል። ሁሉንም በእስክሪኑ ላይ ያለውን መረጃ ለማወቅ ከፈለጉ, በፍላት ሪቪው Flat ይመልከቱ። እያንዳንዱን ነጠላ ዖብጀክት ለመቃኘት ወደፊት እና ወደሗላ ከማለት, ዖብጀክቶች በተዋረድ ተደራጅተው ነው የሚገኙት። ይህ ማለት ዖብጀክቶች ሌላውን obጀክት በውሥጣቸው ሥለሚይዙ ለመመልከት ከፈለጉ በውሥጣቸው ማለፍ ይችላሉ። ለምሳሌ የመዘርዝር ይዘት የዝርዝር አይነቶችን ይይዛል,ሥለሆነም በውሥጡ በማለፍ መመልከት ይቻላል። በመዘርዝር ውሥጥ ከተንቀሣቀሱ, ቀጥል የሚለው እና የቀድሞ የሚለው ወደ ተመሣሣዩ መዘርዝሩ ይወሥዶታል። በተመሣሣዩም የቱል ባር መቆጣጠሪያ ከያዘ, ያው በቱል ባር ውሥጥ አልፈው የቱል ባሩን መቆጣጠሪያ መጠቀም ይችላሉ።
በዖብጀክት ለመቃኘት የሚቀጥሉትን ቁልፎች ይጠቀሙ:
ሥያሜ | የዴስክቶፕ ቁልፍ | የላፕቶፕ ቁልፍ | መግለጫ |
---|---|---|---|
ወቅታዊውን ዖብጀክት ማሣወቅ | NVDA ድምር numpad5 | NVDA ድምር control ድምር I | አሁን ያለውን ቃኚ ዖብጀክት ሪፖርት ያደርጋል። ሁለት ግዜ መታመታ ሢያደርጉ ፊደል በፊደል መረጃውን ሪፖርት ያደርጋል, እንዲሁም ሶስት ግዜ መታመታ ካደረጉ የዖብጀክቱን ሥም እና ዋጋ ወደ ክሊፕቦርድ ኮፒ ያደርጋል. |
ወደ ዖብጀክት ይዞታ አንቀሣቅሥ | NVDA ድምር numpad8 | NVDA ድምር shift ድምር I | ዖብጀክት ቃኚውን ወደ ወቅታዊው ዖብጀክት ይዞታው ያንቀሣቅሠዋል |
አንቀሣቅሥ ወደ ቀድሞው ዖብጀክት | NVDA ድምር numpad4 | NVDA ድምር control ድምር J | አሁን ካለበት ወደ ቀድሞው ቃኚ ዖብጀክት ያንቀሣቅሠዋል |
አንቀሣቅሥ ወደ ቀጣዩ ዖብጀክት | NVDA ድምር numpad6 | control ድምር NVDA L | አሁን ካለበት ወደ ቀጣይ ቃኚ ዖብጀክት ያንቀሣቅሠዋል |
አንቀሣቅሥ ወደ መጀመሪያው ዖብጀክት ይዞታ | NVDA ድምር numpad2 | NVDA ድምር shift ድምር comma | ወደ መጀመሪያው የዖብጀክት ይዞታ ለማንቀሣቀሥ, ወቅታዊውን ዖብጀክት ቃኚ ያንቀሣቅሣል |
አንቀሣቅሥ ወደ ዖብጀክት ትኩረት | NVDA ድምር numpadMinus | NVDA ድምር backspace | ዖብጀክቱን የሲስተሙ ትኩረት ወደ አለበት ያንቀሣቅሠዋል, እንዲሁም ደግሞ የመገምገሚያውን ጠቋሚ ወደ ሲስተም ጠቋሚ ስፍራ ያሢዘዋል, እሥከታየ ድረሥ |
የዖብጀክቱን ቃኚ ስራ ላይ ማዋል | NVDA ድምር numpadEnter | NVDA ድምር enter | አሁን ያለውን የዖብጀክት ቃኚ ጀምር ማለት (በቀላሉ በማውስ ጠቅ እንደማድረግ ወይንም የእስፔስ ቁልፍን መጨቆን የሲስተሙ ትኩረት እሥካለ ድረሥ) |
አንቀሣቅሥ የሲስተሙን ትኩረት ወይንም ጠቋሚ ወደ ክለሳ አቅጣጫ | NVDA ድምር shift numpadMinus | NVDA ድምር shift backspace | አንዴ ሢጨቁኑት የሲስተሙ ትኩረት ወደ ዖብጀክት ቃኚው ይንቀሣቀሣል, ሁለት ግዜ መታመታ ሢያደርጉት የሲስተሙን ጠቋሚ ወደ ክለሣ ጠቋሚ አቅጣጫ ያንቀሣቅሣል |
የዖብጀክት ቃኝ ዙሪያ መጠን ማሣወቅ | NVDA ድምር numpad Delete | NVDA ድምር delete | የዖብጀክት ቃኝ ዙሪያ መጠን በእሥክሪኑ ላይ በፐርሰንቴጅ ያሣውቃል (በተጨማሪም የግራ እና የከፍታ እርቀቱን ከእሥክሪኑ ላይ, እንዲሁም ሥፋቱን እና ቁመቱን) |
ማሣሠቢያ: የነምፓዱ ቁልፍ መቆለፍ አለበት በደንቡ ለመጠቀም።