ኤንቪዲኤ 2021.3beta2 የኪቦርድ ማዘዣዎች ፈጣን ማጣቀሻ

ከNVDA ጋር መጀመር

መሠረታዊ የቁልፍ ማዘዣዎች

ሥያሜ ቁልፍ መግለጫ
አቁም ንግግር ኮንትሮል ወዲያው ንግግር ያሥቆማል
መግቻ ንግግር ሽፍት ወዲያው ይገታል ንግግር። ደግመው ሢጫኑትከተገታበት ቦታ ጀምሮ መነጋገር ይጀምራል (መግቻው አሁን የተተከለው ሢnneተሣይዘር የሚደግፈው ከሆነ)
NVDA ሜኑ NVDA ድምር N ይከፍታል የNVDA ሜኑ ይኸውም አማራጭን አክሰስ ለማድረግ, ቱልስ እና እገዛ ወዘተ
የንግግር መለዋወጫ ሁኔታ NVDA ድምር S የንግግሩን ሁኔታ በእነዚህ መካከል ይለዋውጣል, ንግግር, ጢጥ እና ማጥፋት።
የእገዛ ኪቦርድ መለዋወጫ ሁኔታ NVDA ድምር 1 በእዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ማንኛውንም ቁልፍ ቢመቱ ስለ ቁልፉ, መግለጫ እና ማንኛውንም ከNVDA ጋር የተያያዙትን ማዘዣዎች ይነግሮታል።
ማቋረጥ NVDAን NVDA ድምር Q NVDAን ይዘጋል
በቀጣዩ ቁልፍ ውሥጥ ሥለማለፍ NVDA ድምር F2 ምንም እንኳን ቁልፉ እንደ NVDA እንዲሰራ ቢታዘዝ, በእዚህ ሁኔታ ቁልፉ እንደማንኛውም ቁልፍ ይሰራል
አፕሊኬሽኑን አሣርፍ በሚለው ሁኔታ በመለዋወጥ ማብራት እና ማጥፋት NVDA ድምር ሽፍት ድምር S ይህ ትእዛዝ NVDAን በማሣረፍ, የንግግርም ሆነ የብሬል ስራ ያቋርጣል። ይኸውም ሌላ የእሥፒች ሢንተሣይዘር ካለ ለመጠቀም ያሥችላል። ነገርግን ይህ ትእዛዝ እንደገና ከተሠጠ, ወደ ቀድሞው ስራው ይመለሣል

የሢሥተሙን መረጃ ስለማሣወቅ

ሥያሜ ቁልፍ መግለጫ
ቀን እና ሠዐት ማሣወቂያ NVDA ድምር ኤፍ 12 አንዴ ሢመቱት ሠዐት ይነግራል, ሁለተኛ በፍጥነት ሢመቱት ቀን ይነግራል
የባትሪውን የጉልበት አቅም ማሣወቂያ NVDA ድምር ሽፍት ድምር B የባትሪውን ጉልበት ምንም እንኳን ኤሌትሪክ ተሠክቶም ቢሆን ምን ያህል እንደሞላ በፐርሠንት ያሣውቃል
በክሊፕቦርድ ላይ ያለውን ቴክስት ማሣወቂያ NVDA ድምር C በክሊፕቦርዱ ላይ ማንኛውም ትቴክስት ከተቀመጠ ያሣውቃል።

በNVDA መቃኘት

ዖብጀክቶች

ሥያሜ ቁልፍ መግለጫ
አሁን በትኩረት ላይ ያለውን መግለጽ NVDA ድምር ታብ ወቅታዊውን ዖብጀክት ያሣውቃል ወይንም የሲስተሙን ትኩረት ይቆጣጠራል። ሁለት ግዜ መታመታ ሢደረግ መረጃውን ፊደል በፊደል ያነባል
ያሉበትን ሁኔታ ገላጭ NVDA ድምር T ይህንን ቁልፍ ሢጨቁኑ, NVDA አሁን ዊንዶው ያለበትን ሁኔታ ይገልጻል። በፍጥነት ሁለት ግዜ መታመታ ሢያደርጉ መረጃውን ፊደል በፊደል ያነባል። ሶስተኛ ግዜ መታመታ ሢያደርጉ, መረጃውን ወደ ክሊፕቦርድ ይገለብጣል
ተከፍቶ ስራ ላይ ያለውን ዊንዶው አንባቢ NVDA ድምር B ተከፍቶ በስራ ላይ ያለውን የሁሉንም የዊንዶው መቆጣጠሪያ ያነባል (ጠቃሚ ነው ለዳያሎጎች።)
ያሉበትን ሁኔታ ማሣወቂያ NVDA ድምር END ያሉበትን ሁኔታ NVDA ካገኘ ያሣውቃል። ደግሞም ዖብጀክት መቃኛውን ወደ እዚሁ ሥፍራ ያንቀሳቅሠዋል
ሥያሜ ቁልፍ መግለጫ
ሁሉንም ተናገር NVDA ድምር ቀስት ወደ ታች የሲስተሙ ጠቋሚ ከሚጀምርበት አንሥቶ ጽሁፉ እሥከሚያበቃበት ድረሥ ያነባል
አንብብ ያረፈበትን መሥመር NVDA ድምር ቀስት ወደ ላይ የሲስተሙ ጠቋሚ ያረፈበትን መሥመር ያነባል። ሁለት ግዜ መታመታ ሲደረግ, መሥመሩን ፊደል በፊደል ያነባል።
አንብብ አሁን የተመረጠውን ጽሁፍ NVDA ድምር ሽፍት ድምር ቀስት ወደ ላይ NVDA ማንኛውንም አይነት የተመረጠ ጽሁፍ ያነባል

ወደ ሠንጠረዥ ውሥጥ ሢገቡ የሚጠቀሙባቸው የማዘዣ ቁልፎች ደግሞ እነሆ:

ሥያሜ ቁልፍ መግለጫ
ወደ ቀዳማይ ኮለም አንቀሣቅሥ ቁጥጥር ድምር ዖልት ድምር ግራ ቀስተኛ የሲስተሙን ጠቋሚ አሁን ካለበት ስፍራ ወደ ቀዳማይ ኮለን ያንቀሣቅሣል (ነገርግን ባለበት ተራ መሥመር ውሥጥ ነው)
ወደ ታችኛው ኮለም አንቀሣቅሥ ቁጥጥር ድምር ዖልት ድምር ቀኝ ቀስተኛ የሲስተሙን ጠቋሚ አሁን ካለበት ስፍራ ወደ ታችኛው ኮለን ያንቀሣቅሣል (ነገርግን ባለበት ተራ መሥመር ውሥጥ ነው)
ወደ ቀዳማይ ተራ መሥመር አንቀሣቅሥ ቁጥጥር ድምር ዖልት ድምር ቀስት ወደ ላይ የሲስተሙን ጠቋሚ አሁን ካለበት ስፍራ ወደ ቀዳማይ ተራ መሥመር ያንቀሣቅሣል (ነገርግን ባለበት ኮለን ውሥጥ ነው)
ወደ ታችኛው ተራ መሥመር አንቀሣቅሥ ቁጥጥር ድምር ዖልት ድምር ቀስት ወደ ታች የሲስተሙን ጠቋሚ አሁን ካለበት ስፍራ ወደ ታችኛው ተራ መሥመር ያንቀሣቅሣል (ነገርግን ባለበት ኮለን ውሥጥ ነው)

የዖብጀክት ቅኝት

ሥያሜ የዴስክቶፕ ቁልፍ የላፕቶፕ ቁልፍ መግለጫ
ወቅታዊውን ዖብጀክት ማሣወቅ NVDA ድምር numpad5 NVDA ድምር control ድምር I አሁን ያለውን ቃኚ ዖብጀክት ሪፖርት ያደርጋል። ሁለት ግዜ መታመታ ሢያደርጉ ፊደል በፊደል መረጃውን ሪፖርት ያደርጋል, እንዲሁም ሶስት ግዜ መታመታ ካደረጉ የዖብጀክቱን ሥም እና ዋጋ ወደ ክሊፕቦርድ ኮፒ ያደርጋል.
ወደ ዖብጀክት ይዞታ አንቀሣቅሥ NVDA ድምር numpad8 NVDA ድምር shift ድምር I ዖብጀክት ቃኚውን ወደ ወቅታዊው ዖብጀክት ይዞታው ያንቀሣቅሠዋል
አንቀሣቅሥ ወደ ቀድሞው ዖብጀክት NVDA ድምር numpad4 NVDA ድምር control ድምር J አሁን ካለበት ወደ ቀድሞው ቃኚ ዖብጀክት ያንቀሣቅሠዋል
አንቀሣቅሥ ወደ ቀጣዩ ዖብጀክት NVDA ድምር numpad6 control ድምር NVDA L አሁን ካለበት ወደ ቀጣይ ቃኚ ዖብጀክት ያንቀሣቅሠዋል
አንቀሣቅሥ ወደ መጀመሪያው ዖብጀክት ይዞታ NVDA ድምር numpad2 NVDA ድምር shift ድምር comma ወደ መጀመሪያው የዖብጀክት ይዞታ ለማንቀሣቀሥ, ወቅታዊውን ዖብጀክት ቃኚ ያንቀሣቅሣል
አንቀሣቅሥ ወደ ዖብጀክት ትኩረት NVDA ድምር numpadMinus NVDA ድምር backspace ዖብጀክቱን የሲስተሙ ትኩረት ወደ አለበት ያንቀሣቅሠዋል, እንዲሁም ደግሞ የመገምገሚያውን ጠቋሚ ወደ ሲስተም ጠቋሚ ስፍራ ያሢዘዋል, እሥከታየ ድረሥ
የዖብጀክቱን ቃኚ ስራ ላይ ማዋል NVDA ድምር numpadEnter NVDA ድምር enter አሁን ያለውን የዖብጀክት ቃኚ ጀምር ማለት (በቀላሉ በማውስ ጠቅ እንደማድረግ ወይንም የእስፔስ ቁልፍን መጨቆን የሲስተሙ ትኩረት እሥካለ ድረሥ)
አንቀሣቅሥ የሲስተሙን ትኩረት ወይንም ጠቋሚ ወደ ክለሳ አቅጣጫ NVDA ድምር shift numpadMinus NVDA ድምር shift backspace አንዴ ሢጨቁኑት የሲስተሙ ትኩረት ወደ ዖብጀክት ቃኚው ይንቀሣቀሣል, ሁለት ግዜ መታመታ ሢያደርጉት የሲስተሙን ጠቋሚ ወደ ክለሣ ጠቋሚ አቅጣጫ ያንቀሣቅሣል
የዖብጀክት ቃኝ ዙሪያ መጠን ማሣወቅ NVDA ድምር numpad Delete NVDA ድምር delete የዖብጀክት ቃኝ ዙሪያ መጠን በእሥክሪኑ ላይ በፐርሰንቴጅ ያሣውቃል (በተጨማሪም የግራ እና የከፍታ እርቀቱን ከእሥክሪኑ ላይ, እንዲሁም ሥፋቱን እና ቁመቱን)